Quantcast
Channel: unicef – UNICEF Ethiopia
Viewing all articles
Browse latest Browse all 145

አጣዳፊ ተቅማጥና እና ትውከት /አተት/ በሽታን እንከላከል

$
0
0

የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ በተለያዩ በጥቃቅን በዓይን በማይታዩ ተዋህሲያን አማካይነት አማካይነት የሚከሰት በሽታ ሲሆን ከንጽህና መጓደል በተለይም በተህዋሲያን በተበከሉ ምግቦች፣ የመጠጥ ውሃ እና በሌሎች መተላለፊያ መንገዶች ከሰው ወደ ሰው በከፍተኛ ፍጥነት የሚተላለፍ ነዉ፡፡

በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ በአንዳንድ አካባቢዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በቂ ያለመሆንና በዓለም ላይ በተከሰተዉ የኢሊኖ አየር መዛባት ምክንያት የዉሃ እጥረትና በሌላዉ በኩል የጎርፍ ችግር መኖር እንዲሁም ፣ ከሕብረተሰቡ የአከባቢ፣ የግል፣ የውሃና የምግብ ንጽህና አያያዝና አጠቃቀም ልማድ አለመዳበር ጋር ተያይዞ የተቅማጥ በሽታዎች ስርጭት በየጊዜው እንዲከሰት አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡ በተለይም በጎርፍ ምክንያት ምንጮች፣ ወንዞች፣ የውሃ ጉድጓዶች ስለሚበከሉ በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ይጨምራል፡፡

የአተት ምልክቶች ምንድናቸው ?

በበሽታው የተያዘ ሰው በተደጋጋሚ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ይኖረዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የሰውነት ፈሳሽና ጠቃሚ የሆኑትን ንጥረ ነገሮች መጠን ያዛባል፡፡ በተጨማሪም

  • አጣዳፊ መጠነ ብዙ የሆነ ውኃማ ተቅማጥ
  • ትውከትና ቁርጥማት
  • የአይን መስርጐድ
  • የአፍና የምላስ መድረቅ
  • እንባ አልባ መሆን
  • የሽንት መጠን መቀነስ
  • የቆዳ ድርቀትና መሸብሸብ በመጨረሻም ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ድርቀት በማስከተል ህመምተኛው በወቅቱ ካልታከመ ለሞት ሊያበቃው ይችላል፡፡

አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት የሚያስከትለው ችግር ምንድነው ?

በአተት የተያዘ ሰው ከሰውነቱ ብዙ ፈሳሽ ስለሚወጣ በሽተኛው የሰውነት ድርቀት /Dehydration/ ያስከትልበታል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በአተት የተያዘው ሰው በአጭር ጊዜ ራሱን እንዲስት ያደርገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አፋጣኝ የሕክምና ዕርዳታ ካላገኘ በበሽታው የመሞት አጋጣሚው ሃምሳ ከመቶ /5%/ ነው፡፡ ነገር ግን አስፈላጊው የሕክምና ዕርዳታ ከተደረገለት የመሞት አጋጣሚው ከአንድ ከመቶ /1%/ ወይም ከዚያ በታች ማድረግ ይቻላል፡፡

በሽታውን መለያ መንገዶች

1. ምልክቶቹን በማየት

2. በላብራቶሪ ሊረጋገጥ ይችላል፡፡

ህክምናው

  • የወጣውን ፈሳሽ መተካት ዋናውና ቅድሚያ የሚሰጠው ነው
  • እንደ ተዋህሲያኑ አይነት በባለሙያ የሚሰጥ ህክምናን ተግባራዊ ማድረግ

መከላከያና መቆጣጠሪያ መንገዶች

AWD message in Amharic

  • መፀዳጃ ቤት መገንባትና በአግባቡ መጠቀም
  • ምግብን በሚገባ አብስሎ መመገብ
  • በውኃ /መድሃኒት/ በውኃ አጋር/ የታከመ ውሃ ለመጠጥ መጠቀም ወይም ውኃ አፍልቶና አቀዝቅዞ መጠጣት
  • እጅን በውኃና በሳሙና /በአመድ በደንብ አጥርቶ መታጠብ
    • ከመጸዳጃ ቤት መልስ
    • ምግብ ከማዘጋጀት በፊት
    • ምግብ ከማቅረብ በፊት
    • ምግብ ከመመገብ በፊት
    • ሕጻናትን ካጸዳዱ በኋላ
    • ህጻናትን ጢት ከማጥባት በፊት
    • በበሽታዉ የተያዙ ሰዎችን እነክብካቤ ካደረጉ በኃላ

ማንኛውም ከቤት የሚወጣ ደረቅ ወይም ፈሳሽ ቆሻሻ አካባቢን ወይንም ውኃን እንዳይበክል በአግባቡ ማስወገድ፡፡ ምልክቱ የታየበት ህመምተኛ ፈጥኖ ወደ ህክምና ተቋም በመምጣት ሊታከም ይገባል፡፡

ይህንን መሰረት በማድረግ ሁሉም ህብረተሰብ በሽታዉን በመከላከል ዙሪያ የተሰጡ መልእክቶችን በመተግበር እያንዳንዱ ግለሰብ እራሱንና ቤተሰቡን እንዲሁም አካባቢዉን ሊከላከል ይገባል፡፡



Viewing all articles
Browse latest Browse all 145

Trending Articles